የሀገር ውስጥ ዜና

የአየር ንብረት ፋይናንስ ለታዳጊ ሀገራት ቅድሚያ ፍላጎቶች ምላሽ በሚሰጥ መልኩ ሊቀርብ ይገባል – ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር)

By Hailemaryam Tegegn

November 17, 2026

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 8፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የአየር ንብረት ፋይናንስ ለታዳጊ ሀገራት ቅድሚያ ፍላጎቶች ምላሽ በሚሰጥ መልኩ ሊቀርብ ይገባል አሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና የኮፕ32 ተመራጭ ፕሬዚዳንት ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር)

በኮፕ31 ጉባኤ “ከውጥን ወደ ተግባር፡ በዓለም አቀፍ የአካባቢ ጥበቃ ተቋም፣ በዝቅተኛ የዕድገት ደረጃ ላይ ለሚገኙ ሀገራት ፈንድ እና በልዩ የአየር ንብረት ለውጥ ፈንድ አማካኝነት የገንዘብ ድጋፍ ማሰባሰብ” የተሰኘው የከፍተኛ ኃላፊዎች ውይይት ተካሂዷል፡፡

ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ለታዳጊ ሀገራት የገንዘብ ድጋፍና የቴክኖሎጂ ተደራሽነት ሀገራዊ ውጥኖችን ወደ ተግባር ለመቀየር ወሳኝ ነው፡፡

የአየር ንብረት ፋይናንስ በሚያስፈልገው ደረጃ፣ በተደራሽ መንገዶችና ለታዳጊ ሀገራት ቅድሚያ ፍላጎቶች ምላሽ በሚሰጥ መልኩ እንዲቀርብ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ሀብቶች በቂ በማይሆኑበት ጊዜ ትግበራ እንደሚዘገይና ተጋላጭነት እንደሚባባስ እንዲሁም በጋራ ጥረት ላይ የሚኖረው እምነት እንደሚዳከም ገልጸዋል።

በዓለም አቀፍ የአካባቢ ጥበቃ ተቋም የቤተሰብ ድጋፍን ጨምሮ በዝቅተኛ የዕድገት ደረጃ ላይ ለሚገኙ ሀገራት ፈንድና በልዩ የአየር ንብረት ለውጥ ፈንድን ለማጠናከር የተጀመረውን የሀብት ማሰባሰብ ጥረት አድንቀዋል፡፡

ኢትዮጵያ የኮፕ32 ጉባኤን በአዲስ አበባ ለማስተናገድ በዝግጅት ላይ በምትገኝበት በዚህ ወቅት ከሁሉም አጋሮች ጋር ለመሥራት ያላትን ዝግጁነት አረጋግጠዋል።

#ኢትዮጵያ #ኮፕ_32_ኢትዮጵያ #COP31 #COP32 #COP32ETHIOPIA #fanamediacorporation