አዲስ አበባ፣ ሕዳር 9፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የጤና ተቋማትን አቅም፣ ቴክኖሎጂና አገልግሎት ማሳደግ ጤናማ ኅብረተሰብን የመገንባት ጥረታችን አካል ነው አሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፡፡
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ በባሕር ዳር ከተማ በመጠናቀቅ ላይ የሚገኘውን ምድረ ገነት ጠቅላላ ሆስፒታል ጎብኝተናል ብለዋል።
ከዚህ ቀደም ተቋርጦ የቆየው ይህ ግንባታ ከስድስት ወራት በፊት በአዲስ ውል እንደገና ተጀምሮ ወደ መጠናቀቂያው መድረሱን ገልጸዋል፡፡
ይህ ባለ አምስት ወለል ዘመናዊ የጤና ተቋም ግንባታ ሲጠናቀቅ ወረቀት አልባ በሆነ የጤና መረጃ ሥርዓት የሚመራ ሲሆን፤ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ የተሻለ የጤና አገልግሎት ይሰጣል ነው ያሉት፡፡
ጤናማ ኅብረተሰብ የመፍጠር ጉዞ በቀልጣፋ አገልግሎትና ዘመኑን በዋጀ ስርዓት መከናወን እንዳለበት ገልጸው፤ የጤና ተቋማትን በአቅም፣ በቴክኖሎጂና በአገልግሎት ማሳደግ ጤናማ ኅብረተሰብን ለመገንባት የምናደርገው ቁርጠኛ ጥረት አካል መሆኑን አመልክተዋል።