የሀገር ውስጥ ዜና

የሠራዊቱን ቁመና የሚመጥኑ መሰረተ ልማቶች ግንባታ ተጠናክሮ ይቀጥላል – ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ

By Yonas Getnet

November 19, 2026

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 10፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የመከላከያ ሠራዊቱን ቁመና የሚመጥኑ መሰረተ ልማቶች ግንባታ ተጠናክሮ ይቀጥላል አሉ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ፡፡

በመከላከያ መሐንዲስ ዋና መምሪያ በወለንጪቲ እና በጌጃ የተገነቡ ክፍለ ጦሮች በዛሬው ዕለት በይፋ ተመርቀዋል፡፡

ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ባለፉት ሰባት ዓመታት በተለያዩ አካባቢዎች ከ30 በላይ ዘመናዊ ወታደራዊ ካምፖች ግንባታ ተከናውኗል፡፡

የመከላከያ ሠራዊቱን ቁመና በሚመጥን መልኩ እየተገነቡ የሚገኙ መሰረተ ልማቶች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ነው የገለጹት፡፡

የመከላከያ መሐንዲስ ዋና መምሪያ ኃላፊ ጀነራል ደስታ አብቼ በበኩላቸው፤ መምሪያው ሠራዊቱ ግዳጁን እንዲወጣ የሚያስችሉ ግዙፍ ፕሮጀክቶችን እየገነባ መሆኑን አንስተዋል።

በዛሬው ዕለት የተመረቁት የወለንጪቲ ክፍለ ጦር ጠቅላይ መምሪያ በ22 ሄክታር እንዲሁም የጌጃ ክፍለ ጦር ጠቅላይ መምሪያ ደግሞ በ53 ሄክታር ላይ ማረፋቸውን ተናግረዋል።

የክፍለ ጦሮቹ ግንባታ ከታቀደው ጊዜ አስቀድሞ መጠናቀቁን ገልጸው፤ ወታደራዊ ካምፕና የጤና ተቋማትን ጨምሮ በርካታ አገልግሎቶችን የሚሰጡ ማዕከላትን የያዙ ናቸው ብለዋል፡፡

በፍቅርተ ከበደ