ስፓርት

ታላቁ ሩጫ የኢትዮጵያን ድንቅ እሴቶች በማስተዋወቅ ረገድ የላቀ ሚና እየተጫወተ ነው – ሰላማዊት ካሳ

By Yonas Getnet

November 22, 2026

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 13፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የስፖርት ቱሪዝምን ከማነቃቃት ባለፈ የኢትዮጵያን ድንቅ እሴቶች ለዓለም በማስተዋወቅ ረገድ የላቀ ሚና እየተጫወተ ነው አሉ የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ።

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በዛሬው ዕለት በደመቀ ሁኔታ ተካሂዶ ተጠናቋል።

ሚኒስትሯ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ታላቁ ሩጫ አዲስ አበባ በየዓመቱ የምትደምቅበት ታላቅ ሁነት ነው።

በውድድሩ ላይ ከከተማዋ ነዋሪዎች በተጨማሪ የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ አባላትና ከመላው ሀገሪቱ የተወጣጡ የኅብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፎ በየዓመቱ እየጨመረ መምጣቱን ተናግረዋል።

ይህ የሩጫ ውድድር የኢትዮጵያን በጎ ገጽታ ከማስተዋወቅ ባለፈ፣ ሀገሪቱ ትልልቅ ዓለም አቀፍ ሁነቶችን ማስተናገድ እንደምትችል በተግባር የሚያሳይ መሆኑን አመልክተዋል።

በዘንድሮው ሩጫ ከ60 ሺህ በላይ ሰዎች መሳተፋቸውን ጠቅሰው፤ ውድድሩ በዓለም አቀፍ ደረጃም ትልቅ እውቅና የሚያሰጥ መሆኑን ገልጸዋል።

ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ከታላቁ ሩጫ ጋር በመተባበር ከአዲስ አበባ ባሻገር በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች ላይ የጎዳና ላይ ሩጫዎችን በማዘጋጀት ተደራሽነቱን እያሰፋ መሆኑንም ጠቁመዋል።

ኢትዮጵያ ምድረ ቀደምት ናት ስትባል ቀደምትነቷ በአትሌቲክስም ጭምር መሆኑንና ይህንንም ታሪክና ባህል አስተሳስረን ለዓለም የምንነግርበት ጥሩ መድረካችን ነው ማለታውቸን የዘገውበ ኢዜአ ነው።

#ኢትዮጵያ #ትልቅሀገር #ትልቅሕዝብ #ታላቅርዕይ