ስፓርት

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ተተኪ ስፖርተኞችን ማፍራት ላይ በትኩረት ይሰራል – አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ

By Yonas Getnet

November 22, 2026

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 13፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በቀጣይ ተተኪ ስፖርተኞችን ማፍራት ላይ በትኩረት ይሰራል አሉ የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ መሥራች አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ።

26ኛው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በዛሬው ዕለት “ሩጫዬ ቀለሜ” በሚል መሪ ሐሳብ ከ61 ሺህ በላይ ሰዎች በተሳተፉበት በደመቀ ሁኔታ ተካሂዷል።

አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ ውድድሩን አስመልክቶ በሰጡት አስተያየት እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ ትልልቅ ዓለም አቀፍ ውድድሮችን ማዘጋጀት እንደምትችል በተግባር ታይቷል።

በዘንድሮው ውድድር ከ61 ሺህ በላይ ተሳታፊዎች መሳተፋቸውን ጠቁመው፤ ቀደም ሲል ከነበረው አንጻር ዘንድሮ የተሳታፊዎች ቁጥር መጨመሩንና በአደረጃጀትም የተሳካ ሆኖ መከናወኑን ተናግረዋል።

መርሐ ግብሩ ተተኪ ስፖርተኞችን ለማፍራት ከፍተኛ ፋይዳ እንዳውለ ገልጸው በቀጣይም በዘርፉ ተተኪ ትውልድ ማፍራት ላይ ትኩረት አድርገው እንደሚሠሩ ጠቁመዋል።

በዚሁ መሠረት በዘንድሮው ውድድር ከተለያዩ ትምህርት ቤቶች የመጡ ሦስት ሺህ ተማሪዎች በልዩ ሁኔታ መሳተፋቸውን አስታውቀዋል።

በውድድሩ ሕፃናት፣ ሴቶች፣ ወጣቶች፣ አካል ጉዳተኞች እንዲሁም ከውጭ የመጡ የተለያዩ ሀገራት ዜጎች መሳተፋቸውንም አመልክተዋል።

ታላቁ ሩጫ ተተኪዎችን ለማፍራት፣ ሕዝቡን ለማሳተፍና ወደ ስፖርት እንቅስቃሴ ለማስገባት ሲሠራ መቆየቱን አንስተው ውድድሩ በተሳካ ሁኔታ እንዲከናወን የበኩላውቸን አስተዋጽኦ ላበረከቱ ባለድርሻ አካላት ማመስገናቸውን የዘገው ኢዜአ ነው።