አዲስ አበባ፣ ሕዳር 14፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቡሩንዲ ፕሬዚዳንትና የአፍሪካ ኅብረት የወቅቱ ሊቀመንበር ኤቫሪስት ንዳይሺሚዬ ጋር ተወያይተዋል፡፡
ሁለቱ መሪዎች ከ5ኛው ዓለም አቀፍ የአፍሪካ የሕዝብ ጤና ጉባኤ ጎን ለጎን ባደረጉት ውይይት የሁለትዮሽ ትብብራቸውን ለማስፋት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፥ በቅርብ ጊዜ ያደረግናቸውን ምክክሮች መሠረት በማድረግ የጋራ ቅድሚያ የምንሰጣቸውን ጉዳዮች ለመዳሰስ እድል ሰጥቶናል ብለዋል፡፡
በተጨማሪም የጋራ ቀጣናዊና አህጉራዊ አጀንዳዎቻችንን ወደ ተጨባጭ ተግባራት ለመለወጥ የሚያስችሉ ሀሳቦችን እንድንለዋወጥ አስችሎናል ነው ያሉት፡፡