የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከዩጋንዳ ምክትል ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ

By Hailemaryam Tegegn

November 23, 2026

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 14፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከዩጋንዳ ምክትል ፕሬዚዳንት ጄሲካ አሉፖ ጋር ጋር ተወያይተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፥ ከ5ኛው ዓለም አቀፍ የአፍሪካ የሕዝብ ጤና ጉባኤ ጎን ለጎን ከምክትል ፕሬዚዳንቷ ጋር መወያየታቸውን ገልጸዋል፡፡

ውይይታችን ታሪካዊ ግንኙነታችንን ወደ ላቀ የሁለትዮሽ ትብብር እና የጋራ ቀጣናዊ እድገት መለወጥ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነበር ብለዋል።