የሀገር ውስጥ ዜና

ህብረተሰቡ በችግር ወቅት ያዳባረውን የመተባበር እሴት አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል- የሀዋሳ ከተማ ም/ከንቲባ

By Tibebu Kebede

September 06, 2020

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ህብረተሰቡ በችግር ወቅት ያዳባረውን የመተባበርና የመደገፍ እሴት አጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ የሃዋሳ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ ገለፁ።

በሃዋሳ ከተማ በሰብዓዊ ድጋፍና ልማት ላይ የሚንቀሳቀሰው “ሴንተር ኦፍ ኮንሰርን” የተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅት በከተማዋ ባለሃብቶችንና ድርጅቶችን በማስተባበር በዝቅተኛ ኢኮኖሚ ላይ ለሚገኙ አ1 ሺህ የህብረተሰብ ክፍሎች ማዕድ የማጋራት ተግባር አከናውኗል።