አዲስ አበባ፣ ሕዳር 14፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የድምፃዊ ሚኪያስ ቸርነት ሥርዓተ ቀብር ዛሬ በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈጽሟል።
ድምፃዊው በወልቂጤ ከተማ የሙዚቃ ሥራውን እያቀረበ በነበረበት ወቅት ባጋጠመው ድንገተኛ ሕመም ሕይወቱ ማለፉ ይታወሳል።
የኔ ደሃ፣ አሁን ገባኝ፣ ግርማ ሞገሴ ነሽ፣ ኪያዬ እና አትጨናነቅ በተሰኙ ዜማዎቹ ተወዳጅ የነበረው ድምጻዊ ሚኪያስ ቸርነት ሰላም አላት እና 10 ከ10 ይገባሻል የተሰኙ ሁለት አልበሞችን ጨምሮ በርካታ ነጠላ ዜማዎችን ለሙዚቃ አድማጮች አቅርቧል።
ድምፃዊ ሚኪያስ ቸርነት ባለትዳር ሲሆን፣ የሁለት ወንድና የሁለት ሴት ልጆች አባት ነበር።
ድምፃዊው በ45 ዓመቱ ኅዳር 12 ቀን 2019 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።