ስፓርት

91ኛውን የአየር ኃይል ምስረታ ቀን ምክንያት በማድረግ የቢሾፍቱ የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድር ይካሄዳል

By Yonas Getnet

November 24, 2026

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 15፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) 91ኛውን የኢትዮጵያ አየር ኃይል ምስረታ በዓል አስመልክቶ ሁለተኛው የቢሾፍቱ 10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ይካሄዳል።

የኢትዮጵያ አየር ኃይል በዛሬው ዕለት በሰጠው መግለጫ እንደገለጸው፤ ውድድሩ “አየር ኃይላችን መመኪያችን” በሚል መሪ ሐሳብ ሕዳር 20 ቀን 2019 ዓ.ም በቢሾፍቱ ከተማ ይካሄዳል።

በውድድሩ 800 ፕሮፌሽናል አትሌቶችን ጨምሮ ከ10 ሺህ በላይ ሰዎች ይሳተፋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም ተገልጿል።

በውድድሩ መሳተፍ የሚፈልጉ ሰዎች በአትሌቲክስ ፌዴሬሽን፣ በአዲስ አበባ ስታዲየም እና በጃንሜዳ በመገኘት መመዝገብ እንደሚችሉ ተመላክቷል።