የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመጀመሪያ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች፡-

By Yonas Getnet

November 26, 2026

👉 ከአገልግሎት ዘርፍ ባለፉት ሶስት ወራት 2 ነጥብ 9 ቢሊየን ዶላር አግኝተናል፤ ይህም ከአምናው ጋር ሲነጻጸር 27 በመቶ እድገት አለው።

👉 ከውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ባለፉት ሦስት ወራት 1 ነጥብ 28 ቢሊየን ዶላር ማግኘት ተችሏል፤ ይህም ከአምናው ተመሳሳይ ጊዜ ሲወዳደር 34 በመቶ እድገት አለው።

👉 በወጪ ንግድ፣ በአገልግሎት ዘርፍ፣ በውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት፣ በሃዋላ እንዲሁም በልዩ ልዩ የሚገኙ ገቢዎች ከፍ ብለው ታይተዋል።

👉 የገቢ ንግድን በሚመለከት ባለፉት ስድስት ወራት 6 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር ወጪ አውጥተናል።

👉 ከዚህ ውስጥ የነዳጅ ድርሻ ከባለፈው ዓመት በ70 በመቶ ብልጫ አሳይቷል፡፡

👉 ነዳጅ ዘንድሮ በነበረው ቀውስ ምክንያት ወደብና በቂ ዲፖ የሌላት ሀገር እንደ ሀገር ሳትቆም መደጎም ብቻ ሳይሆን አብቃቅተን ተጠቅመን ያለፍንበት ሁኔታ በከፍተኛ ደረጃ ምስጋና ሊቸረው የሚገባ ተግባር ነው።

👉 በቂ ዲፖ የለንም፣ ገዝተን አናከማችም፣ የነዳጅ ዝውውር ታውቋል፣ ዋጋ ጨምሯል።

👉 በዚያ ሁሉ ችግር ውስጥ ግን ነዳጅ በድጎማ ማምጣታችን ብቻ ሳይሆን ያስተዳደርንበት መንገድ በራሱ ከፍተኛ ምስጋና የሚቸረው ተግባር ነው።

👉 ከዚህ አንጻር የንግድ ሚኒስቴር፣ የነዳጅ ድርጅት ባለስልጣንና የነበረው ስቲሪንግ ኮሚቴ ለሰራው ስራ ከፍተኛ ምስጋና ማቅረብ እፈልጋለሁ።

👉 የኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሪ ክምችት ከማሻሻያው በፊት በከፍተኛ ደረጃ ተመናምኖ እንደነበር ይታወቃል።

👉 ባለፉት ጥቂት ዓመታት ከማሻሻያው ወዲህ ከ20 እጥፍ በላይ አድጓል። የውጭ ምንዛሪ ክምችት ችግር ከሞላ ጎደል ተቃልሏል ማለት ነው።

በቴዎድሮስ ሳህለ