የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመጀመሪያ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች፡-

By tigist gizachew

November 26, 2026

👉 ለመጀመሪያ ጊዜ በሚባል ደረጃ ተጨማሪ ብድር ሳንጠይቅ በገቢያችን ልክ ወጪ ለማውጣት የሞከርንበት ጊዜ ነው፤ ከዚህ ወጪ ውስጥ 88 ቢሊየን ብር ገደማ ለእዳ ክፍያ የዋለ ነው።

👉 ገቢ ከጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት አንጻር አሁንም ዝቅተኛ ነው ተጨማሪ ገቢ ያስፈልጋል፡፡

👉 ከ100 ሚሊየን ህዝብ በላይ ባለበት ሀገር 10 ሺህ የማይሞላ ግብር የሚከፍልበት ሀገር የ10 ሺህ ሰው ግብር የ100 ሚሊየን ህዝብ ፍላጎት እንዴት ሊያሟላ እንደሚችል መገመት ከባድ አይደልም።

👉 ኢትዮጵያ ውስጥ ግብር የሚከፍሉ ኃይሎች በጣም ጥቂት ናቸው፤ የግብር መሰረቱን ማስፋት ያስፈልጋል ሲባል ሰው ከሰራው ስራ ውስጥ በየደረጃው መጠነኛ የሆነ ግብር መክፈል ካልቻለ መሰረተ ልማት ማምጣት አይቻልም።

👉 መሰረተ ልማት ለመገንባት ግብር ካልመጣ መንግሥት የሚጠበቅበትን በበቂ ለመከወን ይቸገራል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የግብር መሰረት በዚህ መልኩ ማየት ከአጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት እየገባ ያለውን ገቢ ማየት ያስፈልጋል፡፡

👉 ስራ የሚሰሩ ግብር የሚከፍሉ ሰዎች በአንድ በኩል ግብር መክፈል ክብር መሆኑን ማወቅ አለባቸው፤ በሌላ በኩል ስራ በሰራን ቁጥር በዛው ልክ የምናጋራው የሀብት ልክ መኖሩን ማወቅ ያስፈልጋል።

👉 ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ነጋዴዎች ግብር መክፈል ላይ የሚቸገሩት እንጂ በተለያየ መንገድ ደግፉ ቢባሉ መንግሥት አካውንት በማያደርጋቸው መንገዶች በጣም በርካታ ብር ያወጣሉ፡፡

👉 ግብር የመክፈል ፍላጎቱ ከመንግሥት ሰራተኞች አንጻር ሲታይ ታማኝ ግብር ከፋይ በጣም ውስን ነው፤ አስበው የሚከፍሉ በጣም ጥቂት እንዳሉ ይታወቃል፡፡ አብዛኛው በግብር ስወራ ላይ ነው ጊዜውን የሚያባክነው፤ ይህንን በአሰራር ማሻሻልና መቆጣጠር ያስፈልጋል፡፡

👉 ከእዳ ሽግሽግ አንጻር ሪፎርሙ እስከ 2028 ወደ መካከለኛ ደረጃ እናወርዳለን የሚል የነበረ ቢሆንም ዘንድሮ በተሰራው ስራ በአጠቃላይ የኢትዮጵያ የእዳ ደረጃ ከነበረበት ከፍተኛ ስጋት ወደ መካከለኛ ወርዷል፡፡ ይህም የሪፎርሙ ትልቅ ስኬት ነው፡፡

#ኢትዮጵያ #ትልቅሀገር #ትልቅሕዝብ #ታላቅርዕይ

በትዕግስት ግዛቸው