👉 የዋጋ ንረት ባለፈው ዓመት አጋማሽ ድረስ በተሰራው አመርቂ ስራ ወደ ነጠላ አሃዝ ገብቶ እንደነበር ይታወሳል፤ ልክ የኢራኑ ግጭት ሲፈጠር ከዓለም አቀፍ የዋጋ ንረት ምክንያት መልሶ ወደ 14 ነጥብ 7 በመቶ አሻቅቧል፡፡
👉 ከስድስት ወር በፊት የዋጋ ንረትን ጉዳይ የምናወራው ኢትዮጵያ ላይ ነበር፤ አሁን ግን በግጭቱ ምክንያት የዋጋ ንረት አሜሪካና አውሮፓን ጨምሮ በየትኛውም የዓለም ክፍል ባሉ ሀገራት ውስጥ በስፋት የሚታይ ችግር ሆኗል።
👉 ለአብነትም ነዳጅን ብንወስድ በአንድ ሊትር 90 ብር ገደማ ጭማሪ አለ፤ ያም ሆኖ ወደብ የሌላት ሀገር ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ ውስጥ ካሉ ሀገራት ጋር ስትወዳደር በጣም በዝቅተኛ ዋጋ ነዳጅ የምታቀርብ ሀገር ናት።
👉 ለምሳሌ አንድ ሊትር ነዳጅ በኬንያ 1 ነጥብ 7 ዶላር፣ በጅቡቲ 1 ነጥብ 77 ዶላር፣ በዩጋንዳ 1 ነጥብ 57 ዶላር፣ በታንዛንያ 1 ነጥብ 53 ዶላር እንዲሁም በሩዋንዳ ከሁሉም ከፍ ብሎ 1 ነጥብ 99 ወይም 2 ዶላር በሊትር ያወጣል።
👉 የእኛን የወሰድን እንደሆነ የመንግሥት ተመን ለአንድ ሊትር 1 ነጥብ 04 ዶላር ነው።
👉 ይህ በምስራቅ አፍሪካ ካሉ ሀገራት በሙሉ ሲታይ በጣም ዝቅተኛው ነው፤ አንዳንዶች እጥፍ በሚባል ደረጃ ይሄዳሉ።
👉 በዚህም በተደረገው ድጎማ የነዳጅ ተቋሙ ባለፉት ስድስትና ሰባት ወራት ወደ 480 ቢሊየን ብር እዳ ተጨማሪ እዳ ተሸክሟል።
👉 ይህ እዳ እንዳለ ሆኖ ወደ ህዝብ ማሻገር ችግር ያስከትላል፤ በተቻለ መጠን አንዳንድ ነገር ቀንሰን ያንን ጊዜያዊ ችግር እንደ መንግስት መሸከም ይሻላል የሚል ሀሳብ ነበር።
👉 በተወሰነ ደረጃ ዋጋን ወደ ህዝብ ማውረድ ካልተቻለ በአንድ ሊትር 90 ብር እየደጎምን ማስቀጠል እንቸገራለን።
👉 አንዱ ችግር ድጎማ የሚሰጣቸው ሰዎች ድጎማ የሚገባቸውና ድጎማ የማይገባቸው መሆናቸውን ለመለየት ስርዓት መፍጠር ባለመቻላችን ለኩባንያዎች፣ ለውጭ ኢምባሲዎች ጭምር ነው ይሄ ድጎማ የሚሰጠው።
👉 ማንም ነዳጅ የሚገዛ ሰው ኢትዮጵያ ውስጥ በዚሁ ዋጋ ይገዛል፤ ይሄ ተገቢ ስላልሆነ በዚያ መንገድ መቀጠል፤ እየታየ ማሻሻያዎች ይደረጋሉ።
👉 ለዚህ አንዱ ምክንያት ሎጂስቲክስ ነው፤ የመርከቦች ዝውውር መታወኩ ከፍተኛ ችግር አምጥቷል።
👉 ኢትዮጵያ በቂ ነዳጅ ማከማቻ ዲፖ መገንባት አለባት።
👉 ኢትዮጵያ ከጅቡቲ ወደብ በቦቴ የምታመላልሰው ነዳጅ ከፍተኛ ኪሳራ ያስከትላል፤ ኮንትሮባንድ ይጋለጣል።
👉 ይሄ ችግር ያስተማረን ትምህርትና ኢንቨስት ማድረግ የግድ ያስፈልጋል የሚል ጥሩ ትምህርት ያገኘንበት ነው።
👉 ከዳንጎቴ ኩባንያ ጋር በጋራ በመሆን ከጅቡቲ ወደብ ወደ ኢትዮጵያ የነዳጅ ማስተላለፊያ ቱቦ ለመዘርጋትና እዛም ረዘም ላለ ጊዜ ሊቆይ የሚችል ዲፖ ለመገንባት ሥራ ተጀምሯል፡፡
👉 ይህ በተለይ ዲሞሬጅን በሚመለከት መርከቦች መጥተው ረዘም ላለ ጊዜ ወደብ ላይ ሲቀመጡ ተጨማሪ ወጭ ስለምናወጣ ያን ለመቀነስ በእጅጉ ያግዛል።
👉 ይሄን ችግር ተባብሶ ዜጎቻችንን በከፍተኛ ደረጃ እንዳይጎዳ እንደ መንግስት ከፍተኛ ርብርብ ስናደርግ ቆይተናል።
👉 አንደኛው ድጎማ ነው፣ ነዳጅም ማዳበሪያም፤ ሁለተኛው ከ2ሺህ 400 በላይ የቅዳሜና እሁድ ገበያዎች ኢትዮጵያ ውስጥ ተከፍተዋል።
👉 አርሶ አደሩንና ሸማቹን ለማገናኘት በየከተማ የፈጠርነው የቅዳሜና እሁድ ገበያዎች የዋጋ ግሽበትን ለመቀነስ አዎንታዊ አስተዋጽኦ አለው።
👉 በየጊዜው ምግብ የማጋራት ልምድ ባህል እየሆነ ሲሄድ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ሰዎች በከፍተኛ ደረጃ ድጋፍ ያገኛሉ።
👉 በትምህርት ቤት ምገባውም እንደዚሁ አነስተኛ ገቢ ያላቸው ቤተሰቦች ልጆቻቸውን ለማስተማር የሚፈጠርባቸውን ጫና ለመቀነስ አስተዋጽኦ አለው።
👉 የጀመርነው በምግብ በተሟላ መንገድ በቂ ምግብ ማምረትና የዋጋን ማረጋጋት ስራ ኢነርጂ በበቂ ማምረትና ሎጂስቲክስ ስርዓቱን፣ ባቡሩንና ፈጣን መንገዶችን ጨምሮ መንገዶች በማስፋፋት ምርት ካለበት ፈላጊ ወዳለበት ለማድረስ ሰፊ ስራ የሚጠይቅ ነው፡፡
#ኢትዮጵያ #ትልቅሀገር #ትልቅሕዝብ #ታላቅርዕይ
በቴዎድሮስ ሳህለ