የሀገር ውስጥ ዜና

ታላቁ የመደመር ስትራቴጂ የተዘጋጀው ከትውልድ የሚሻገር የስልጣኔ ጉዞ ያስፈልጋል በሚል ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

By Yonas Getnet

November 26, 2026

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 17፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ታላቁ የመደመር ስትራቴጂ የተዘጋጀው ከመንግሥት እና ከትውልድ የሚሻገር የስልጣኔ ጉዞ ያስፈልጋል በሚል ነው አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የመጀመሪያ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ተገኝተው ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ታላቁ የመደመር ስትራቴጂን በሚመለከት በሰጡት ማብራሪያም፤ ኢትዮጵያ ሃብታም ሆና ዜጎቿ ደሃ የሆኑበትን ሁኔታ እንዴት መቀየር ይቻላል የሚለው መጠናቱን ገልጸዋል።

የት መድረስ እንፈልጋለን የሚለውን የሚቀይሩ ግቦችን አስቀመጥን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ስትራቴጂው በምን አቅም ነው እዛ የምንደርሰው የሚለውን ይዟል፤ አቅጣጫችንንም ጥርት አድርጎ ያሳያል ብለዋል።

ልማት ከመጣ በኋላ ደግሞ እንዴት ይተዳደራል የሚለው መቀመጡን ገልጸው፤ ይሄን ለማድረግ ሀገር የሚገነባበት 15 ሞዴሎች ተቀምጠዋል ነው ያሉት።

ስልጣኔን የምንገነባው ለትውልድ ነው፤ በእኔ እምነት የልጅ ልጆቻችን መሰረቱን ይረግጣሉ፤ ልጆቻቻን ደግሞ ምሶሰውን ይይዛሉ ብለዋል።

ለመገንባት መታደል ጥሩ ነገር መሆኑን ጠቅሰው፤ ገንብቶ ማሸጋገር ጥበብ የሚፈልግ መሆኑን ተናግረዋል።

ይህ ትውልድ ገንቢ ትውልድ መሆኑን በመግለጽ፤ ታላቁ የመደመር ስትራቴጂ ከመንግሥት እና ከትውልድ የሚሻገር የስልጣኔ ጉዞ ያስፈልጋል በሚል የተዘጋጀ ነው ብለዋል።

#ኢትዮጵያ #ትልቅሀገር #ትልቅሕዝብ #ታላቅርዕይ