አዲስ አበባ፣ ሕዳር 18፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት በዛሬው ዕለት ተጀምሯል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ÷ ዛሬ የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባን ጀምረናል ብለዋል፡፡
ስብሰባው በዋናነት በፓርቲው ስትራቴጂካዊ አቅጣጫ እና በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡