የሀገር ውስጥ ዜና

በኤፍራታና ግድም ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የአምስት ሰዎች ሕይወት አለፈ

By Yonas Getnet

November 27, 2026

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 18፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታና ግድም ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የአምስት ሰዎች ሕይወት አልፏል።

አደጋው ዛሬ በወረዳው ሆራ ቀበሌ የተከሰተ ሲሆን፣ ከአምስቱ ሰዎች ሕይወት ማለፍ በተጨማሪ በሌሎች ተሳፋሪዎች ላይ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት አድርሷል።

ከደሴ ከተማ ተነስቶ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ የነበረ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ በጠዋቱ 2 ሰዓት አካባቢ መንገዱን ስቶ ድልድይ ውስጥ በመግባቱ በደረሰው አደጋ እስካሁን የአምስት ሰዎች ሕይወት አልፏል።

በአደጋው የተጎዱ ሰዎች በአጣዬ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የሕክምና እርዳታ እየተሰጣቸው መሆኑን የወረዳው ኮሙኒኬሽን መረጃ አመልክቷል።