የሀገር ውስጥ ዜና

ቦርዱ በትግራይ ክልል ምርጫ ማስፈጸምን አስመልክቶ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሄደ

By tigist gizachew

November 27, 2026

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 18፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በትግራይ ክልል ምርጫ ማስፈጸምን አስመልክቶ ከሀገር አቀፍ እና በክልሉ ከሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎችና ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሂዷል፡፡

የቦርዱ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ስኬታማ ምርጫ በቦርዱ ጥረት ብቻ የሚከናወን ባለመሆኑ ግልጽ፣ ነፃና ገለልተኛ ምርጫ ለማድረግ የባለድርሻ አካላት ተሣትፎ ማረጋገጥ ይገባል፡፡

የውይይቱ ዓላማም ከባለድርሻ አካላት ግብዓት መሰብሰብ መሆኑንና ቀጣይነት እንደሚኖረው እንዲሁም ከሌሎች ባለድርሻ አካላትም ጋር እንደሚደረግ ተናግረዋል።

ፓርቲዎች ራሳቸውን ለምርጫው ማዘጋጀትና ከወዲሁ የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት ለመወጣት ወደ ሥራ እንዲገቡ አስገነዝበዋል፡፡

የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶችም ዜጎች መብታቸውን በማወቅና በመረዳት በምርጫ አንዲሳተፉ ሰፊ ሥራ መሥራት እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል።

ምርጫው የትግራይ ሕዝብ ራሱን በራሱ እንዲያስተዳድር እንዲሁም በሕዝብ ተወካዮችና በፌዴሬሽን ምክር ቤቶች ውክልና እንዲኖረው የሚያስችል መሆኑ ተመላክቷል፡፡