የሀገር ውስጥ ዜና

የትግራይ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ተመሠረተ ‎

By Hailemaryam Tegegn

November 29, 2026

‎አዲስ አበባ፣ ሕዳር 20፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በትግራይ ክልል የሚንቀሳቀሱ 19 የፖለቲካ ፓርቲዎችን ያቀፈ የትግራይ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በይፋ ተመሥርቷል። ‎ ‎በምሥረታ መድረኩ ላይ የአምስት ፓርቲዎች አመራሮች የምክር ቤቱ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ሆነው ተመርጠዋል።

በዚህም መሠረት ‎አቶ ዓምዶም ገብረሥላሴ ሰብሳቢ፣

አቶ ብርሃነ ገብረጻድቅ ምክትል ሰብሳቢ፣ ‎ ‎አቶ ከበደ አሰፋ ደግሞ የምክር ቤቱ ጸሐፊ ሆነው ተመርጠዋል። ‎ ‎አቶ ሀፍቱ ኪሮስ እና አቶ ጉዕሽ ጊደይ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ሆነው ተመርጠዋል።

በአሸናፊ ሽብሩ