የሀገር ውስጥ ዜና

የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ የዓመቱ የፋይናንስ ሚኒስትር ሽልማትን አሸነፉ

By Tibebu Kebede

December 20, 2019

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 10 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ በፋይናንሺያል አፍሪክ መጽሄት የዓመቱ የፋይናንስ ሚኒስትር ሽልማት ተበረከተላቸው።

ፋይናንሺያል አፍሪክ በፓሪስ የሚታተም መጽሔት ሲሆን፥ ትናንት በአቢጃን ከተማ በተካሄደ ስነ ስርዓት የኢፌዴሪ ገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴን የዓመቱ የፋይናንስ ሚኒስትር በማለት ሽልማት አበርክቶላቸዋል።