አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ)የጤና ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች የአብሮነት ቀንን በተለያዩ ሆስፒታሎች በኮቪድ-19 የለይቶ ማከሚያ ማዕከላት ከሚገኙ የህክምና ባለሞያዎችን እና ድጋፍ ሰጭ ባለሙያዎች ጋር አሳልፈዋል።
በዚህም ሃላፊዎቹ በሚሊኒየም የኮቪድ 19 የህክምና ማዕከል ፣በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል፣ በቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ፣በአማኑኔል አዕምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል፣ በዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል፣ በራስ ደስታ ሆስፒታል፣ በኤካ ኮተቤ እና በአለርት ህክምና ማዕከል በመገኘት በልዩ ልዩ የህክምና ክፍል ውስጥ አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙትን የህክምና ባለሞያዎችን እና ድጋፍ ሰጭ ባለሙያዎች ጋር የአብሮነትን ቀን አሳልፈዋል።