አዲስ አበባ ፣ጳጉሜን 3 ፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዲስ ዓመት በዓልን ምክንያት በማድረግ የተጋነነ የዋጋ ጭማሪ እንዳይከሰት እየሰራ መሆኑን የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አስታወቀ።
የቢሮው ሃላፊ አቶ አብዱልፈታ የሱፍ እንዳሉት፥ በተለይ ለበዓሉ አስፈላጊ የሆኑ የግብርናና የኢንዱስትሪ ምርቶች ለሸማቹ በተመጣጠነ ዋጋ እንዲቀርቡ በህብረት ስራ ማህበራት በኩል ጤፍ፣ ሽንኩርት፣ የቁም እንሰሳትና የእንሰሳት ተዋፆኦ ምርቶች ለህብረተሰቡ እንዲሰራጩ እየተደረገ ነው።