ዓለምአቀፋዊ ዜና

የሶማሊያ ጦር በወሰደው እርምጃ 14 የአልሸባብ ታጣቂዎች ተገደሉ

By Meseret Demissu

September 08, 2020

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 3፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሶማሊያ ጦር በወሰደው እርምጃ 14 የአልሸባብ ታጣቂዎች መገደላቸው ተሰምቷል።

የጦር ሀይሉ እርምጃውን የወሰደው ከዋና ከተማዋ ሞቃዲሾ በስተሰሜን 30 ኪሎ ሜትር ርቃ በምትገኘው ባላድ ከተማ የሽብር ቡድኑ ዛሬ ጠዋት ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ ነው ተብሏል።