የሀገር ውስጥ ዜና

ባለፉት 24 ሰዓታት 916 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ17 ሰዎች ሕይወት አልፏል

By Tibebu Kebede

September 09, 2020

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 15 ሺህ 561 የላብራቶሪ ምርመራ 916 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 61 ሺህ 700 መድረሱን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በፌስቡክ ገፃቸው ላይ አስፍረዋል።