የሀገር ውስጥ ዜና

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ ለ508 የህግ ታራሚዎች ይቅርታ ተደረገ

By Feven Bishaw

September 10, 2020

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 5፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የ2013 አዲሱን ዓመት ምክንያት በማረግ ለ508 የህግ ታራሚዎች ይቅርታ መደረጉን የክልሉ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አስታወቀ።

በክልሉ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የሕግ አገልግሎት ዘርፍ ምክትል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ንጋቱ ዓለሙ እንዳሉት፥ በክልሉ በሚገኙ ሶስቱም ማረሚያ ቤቶች ለሚገኙ 508 የሕግ ታራሚዎች ይቅርታ ተደርጓል።