የሀገር ውስጥ ዜና

በኦሮሚያ በ3 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር የሚከናወነው “ጉማታ ጨፌ ቱማ” የተቀናጀ ፕሮጀክት ወደ ትግባራ ተሸጋገረ

By Tibebu Kebede

September 10, 2020

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 5፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኦሮሚያ ክልል በ3 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር የሚከናወነው “ጉማታ ጨፌ ቱማ” የተቀናጀ ፕሮጀክት ወደ ትግበራ መሸጋገር ጀመረ።

የማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ባህላዊ እና ታሪካዊ ችግሮችን ለመቅረፍ ታልሞ የተዘጋጀው “ጉማታ ጨፌ ቱማ” የተቀናጀ ፕሮጀክት በዛሬው እለት የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ እና በምክትል ርዕስ መስተዳድር ማእረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ አቶ አዲሱ አረጋ ጨምሮ ሌሎችም ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት በሱሉልታ ወረዳ ወደ ትግበራ የማሸጋጋር ሂደት ተከናውኗል።