ም/ጠ/ሚ አቶ ደመቀ የአዲስ ዓመት መልካም ምኞት መልዕክት አስተላለፉ

By Tibebu Kebede

September 10, 2020

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 5፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ)  የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የአዲስ ዓመት መልካም ምኞት መልዕክት አስተላለፉ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአዲስ ዓመት የመልካም ምኞት መልዕክታቸው አዲሱ ዓመት “ከትናንት ትምህርት የምንቀስምበት፤ ዛሬን በጽናት የምንሰራበት፤ ነገን በተለወጠ አስተሳሰብ የምንኖርበት ዘመን ይሁንልን” ሲሉ ተመኝተዋል።

“አዲሱ ዓመት ለሁላችንም የምትሆን የበለፀገች ኢትዮጵያን የምንገነባበት እንዲሆን እመኛለሁ” ብለዋል አቶ ደመቀ በመልዕክታቸው።