አዲስ አበባ፣ መስከረም 1፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 8 ሺህ 191 የላቦራቶሪ ናሙና ምርመራዎች 521 ሰዎች የኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።
ይህንንም ተከትሎ በሀገሪቱ በአጠቃላይ እስካሁን ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 63 ሺህ 888 ደርሷል።
በሌላ በኩል 469 ሰዎች ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ እስካሁን ድረስ 24 ሺህ 493 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።
በ24 ሰዓታት ውስጥ የ10 ሰዎች ህይወትም በቫይረሱ ምክንያት አልፏል።
345 ሰዎችም በአሁኑ ወቅት በፅኑ መታመማቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።