የሀገር ውስጥ ዜና

274 ኢትዮጵያውያን ከሳኡዲ አረቢያ ወደ አገራቸወ ተመለሱ

By Tibebu Kebede

September 16, 2020

አዲስ አበባ፣ መስከረም 6፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሳኡዲ አረቢያ ጅዳ ከተማ በተለያዩ ችግር ውስጥ ይኖሩ የነበሩ 274 ኢትዮጵያውያን ዜጎች ዛሬ ወደ አገራቸው ተመልሰዋል።

ኢትዮጵያውያን ዜጎች ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄኔራል አቶ መስፍን ገ/ማርያምን ጨምሮ ከተለያዩ መ/ቤቶች የተወከሉ ባለሙያዎች ተገኝተው አቀባበል አድርገውላቸዋል።