አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኦሮሚያ ክልል ርእስ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ የተመራ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ቡድን በአፋር ክልል በጎርፍ የተጎዱ አካባቢዎችን በመጎብኘት ድጋፍ አደረገ።
የአዋሽ ወንዝ በመሙላት በአፋር ክልል ባስከተለው ተጎርፍ አደጋ በርካቶችን ከቤት ንብረታቸው ማፈናቀሉ ይታወቃል።
በኦሮሚያ ክልል ርእስ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ የተመራው የክልሉ መንግስት የስራ ኃላፊዎች ቡድን በጎርፍ አደጋው ጉዳት ደርሶባቸው ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ዜጎችን ስፍራው ድረስ በመጓዝ ጎብኝተዋል።
በተጨማሪም በጎርፍ ምክንያት ለተፈናቀሉ ዜጎች የተለያዩ የምግብ ግብአቶችና ቁሳቁሶች ድጋፍ ማድረጋቸው ታውቋል።
የአፋር ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ በጉብኝቱ ላይ የተገኙ ሲሆን፥ የኦሮሚያ ክልል መንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተጎጂዎችን በመጎብኘት ላደረጉት ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።