አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በግንባታ ላይ የሚገኘው የእናቶችና ህፃናት ሆስፒታልን ጎበኙ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ አያት አካባቢ በግንባታ ላይ ያለውን የእናቶችና ህፃናት ሆስፒታልን ጎብኝተዋል።
በአዲስ አበባ በ400 ሚሊየን ብር ወጪ እየተገነባ ያለው የእናቶችና ህፃናት ሆስፒታል ግንባታው ተጠናቆ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ስራ እንደሚጀምር መገለጹን ኢዜአ ዘግቧል፡፡