ዓለምአቀፋዊ ዜና

በህንድ በመኖሪያ ህንጻ በደረሰ የእሳት አደጋ የ9 ሰዎች ህይወት አለፈ

By Tibebu Kebede

December 23, 2019

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 13፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በህንድ ዴልሂ ከተማ በደረሰ የእሳት አደጋ የዘጠኝ ሰዎች  ህይወት ማለፉ ተሰምቷል።

በመኖሪያ ሕንፃ ውስጥ በደረሰው የእሳት አደጋ ህይወታቸውን ካጡ ሰዎች በተጨማሪ 10 ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸው የተነገረው።

ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ለህክምና ወደ አከባቢው ሆስፒታል መወሰዳቸው ነው ከስፍራው የወጡ መረጃዎች የሚያመለክቱት።

ምንጭ፡- ሲ.ጂ.ቲ.ኤን