ዓለምአቀፋዊ ዜና

በናይጄሪያ የነዳጅ ማመላለሻ ቦቴ መኪና ላይ በደረሰ ፍንዳታ በትንሹ የ23 ሰዎች ህይወት አለፈ

By Feven Bishaw

September 24, 2020

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 14 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በናይጄሪያ በነዳጅ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ታንከር ላይ ተበከሰተ ፍንዳታ ቢያንስ የ23 ህይወት ማለፉ ተሰማ፡፡

በማእከላዊ ናይጄሪ ኮጊ በምትባል ግዛት አንድ ነዳጅ ታንከር በመፈንዳቱ ተማሪዎችን ጨምሮ ቢያንስ የ23 ሰዎች ህይወት አልፏል።

አደጋው የደረሰው ትላንት በግዛቱ ሎኮጃ አቡጃ በተባለ አውራ ጎዳና ላይ ሲሆን  የነዳጅ ታንከር የጫነው ተሽከርካሪ ፍሬን በመበጠሱ እና ከአምስት መኪኖች ጋር በመጋጨቱ ነው ተብሏል።

የአከባቢው ባለ ስልጣናት እንደተናገሩትም ታንከሩ በመንገዱ ላይ ወድቆ ወዲያውኑ ቢያንስ ሁለት ሞተር ብስክሌቶችን ፣ አምስት መኪናዎችን እና ሶስት ባለሶስት እግርተሸከርካሪዎችን አቃጥሏል ብሏል።

በዚህም የተሽከርካሪዎቹ ተሳፋሪዎች እና መንገደኞች በሙሉ በእሳት ቃጠሎ ተጎድተዋል ነው የተባለው።

የግዛቱ  አስተዳዳሪ በሰጡት መግለጫ በነዳጅ ማመላለሻ ፍንዳታ በተነሳው የእሳት አደጋ በሰው ሕይወት እና በንብረቶች እና ላይ ደረሰው አሰቃቂ አደጋ እንዳዘኑ ገልፀዋል።

ከስፍራው የወጡ ዘገባዎች እንደሚያመለክቱት  የተወሰኑ የግዛቱ የፖሊ ቴክኒክ ተማሪዎች፣ የአከባቢው የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎችን የሚያጓጉዙ የትምህርት ቤት አውቶብሶች እና በመንገዱ የሚያልፉ ነዋሪዎች በፍንዳታው በተነሳው ቃጠሎ ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡

ምንጭ፡-ሲ.ጂ.ቲ.ኤን እና አልጀዚራ