አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ትምህርት ሚኒስቴር ሁለት የግል ትምህርት ቤቶችን በጊዜያዊነት ማገዱን አስታወቀ፡፡
እገዳው የተላለፈባቸው አንድነት ኢንተርናሽናል እና ሄሌኒክ-ግሪክ ማህበረሰብ ትምህርት ቤቶች መሆናቸው ተገልጿል፡፡
ትምህርት ቤቶቹ የታገዱት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ተከትሎ ትምህርት ሚኒስቴር ያወጣውን የክፍያ መመሪያ ተላልፈው በመገኘታቸው ነው ተብሏል፡፡
አገዳ የተላለፈባቸው የወላጅ ኮሚቴዎች ተደጋጋሚ አቤቱታ በማቅረባቸው ተከትሎ ነው ተብሏል፡፡
ትምህርት ቤቱ ከዛሬ ጀምሮ ሚኒስቴሩ ያወጣውን መመሪያ ከወላጅ ኮሚቴ ጋር በመነጋገር ፈጥነው ሪፖርት እስኪያደርጉ ድረስ ምንም ዓይነት የትምህርት ስራ እንዳይሰሩ መታገዳቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡