የሀገር ውስጥ ዜና

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ሆረ ፊንፊኔ እና የሆረ አርሰዲ በዓል በሰላም እንዲጠናቀቅ አስተዋጽዖ ላደረጉ አካላት ምስጋና አቀረቡ

By Feven Bishaw

October 04, 2020

አዲስ አበባ፣ መስከረም 24፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሆረ ፊንፊኔ እና የሆረ አርሰዲ በዓል በሰላም እንዲጠናቀቅ አስተዋጽዖ ላደረጉ አካላት ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ አስተዋጽዖ ላደረጋችሁ አባገዳዎች፣ ሲንቄዎች ፣ወጣቶች ፣ርዕሳነ መስተዳድሮች ፣ የጸጥታ ተቋማት፣ አጠቃላይ የበዓሉ ታዳሚዎች እና ሚዲያዎች በዓሉ በሰላም ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅበት ሰዓት ድረስ ላደረጋችሁት አስተዋጽኦ ምስጋናዬን አቀርባለሁ ነው ያሉት።