የሀገር ውስጥ ዜና

በሳዑዲ አረቢያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ዜጎች ደህንነት መጠበቅ ዙሪያ ውይይት ተደረገ

By Meseret Demissu

October 06, 2020

አዲስ አበባ ፣መስከረም 26 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሳዑዲ አረቢያ የኢትዮጵያ አምባሳደር አብዱልአዚዝ ከሳዑዲ አረቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄኔራል አምባሳደር ሳሚ ሳልህ ጋር በኢትዮጵያውያን ዜጎች ደህንነት መጠበቅ ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።

አምባሳደር አብዱላዚዝ ውይይቱን ያደረጉት ሰሞኑን በሳኡዲ አረቢያ የሚኖሩ ዜጎች በአንዳንድ አካባቢዎች በአፈሳ ለእስር መዳረጋቸውን ተከትሎ ነው ተብሏል።