ዓለምአቀፋዊ ዜና

ከአጠቃላይ የአለም ህዝብ በግምት 10 በመቶው በኮሮና ቫይረስ ተይዞ ሊሆን ይችላል- የአለም ጤና ድርጅት

By Meseret Awoke

October 06, 2020

አዲስ አበባ፣ መስከረም 26፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ከአጠቃላይ የአለም ህዝብ በግምት 10 በመቶው በኮሮና ቫይረስ ተይዞ ሊሀሆን እንደሚችል የአለም ጤና ድርጅት አስታውቋል፡፡

ይህም ማለት ከ10 ሰዎች መካከል አንዱ በኮቪድ-19 ሊያዝ ይችላል ማለት ነው፡፡

በዚህም አብዛኛው የአለም ህዝብ ለቫይረሱ ይበልጥ ተጋላጭ እንደሚሆን ድርጅቱ አስታውቋል፡፡

በደቡብ ምስራቅ እስያ አንዳንድ አካባቢዎች ወረርሽኙ እየጨመረ መሆኑን የተናገሩት በድርጅቱ የድንገተኛ ጉዳዮች ዋና ኃላፊ ዶክተር ማይክ ራያን በአውሮፓ እና በምስራቅ ሜድትራንያን አካባቢዎች ደግሞ የወረርሽኙ ስርጭት እና የሞት መጠን እየጨመረ ተናግረዋል፡፡

ከአጠቃላይ የአለም ህዝብ 10 በመቶው በኮሮና ቫይረስ ተይዞ ሊሆን ይችላል የሚል ግምት ቢኖርም እንደየ ሃገራቱ፣ ከገጠር ከተማ እንዲሁም ቡድኖች እንደሚለያይ ገልጸዋል፡፡

”በአሁኑ ወቅትም ወደ አስቸጋሪ ጊዜ እየገባን ነው ፤ በሽታው መስፋፋቱን ቀጥሏል” ሲሉም ተናግረዋል ፡፡

ምንጭ፡- ሲጂቲኤን