አዲስ አበባ፣ መስከረም 28፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)በሶማሌ ክልል የተገነባው የፀሀይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት መሆኑ ተገለፀ።
በምርቃ ስነ ስርዓቱ ላይ የሶማሊ ክልል ምክትል ርዕስ መስተዳደር አቶ ሙስጠፌ መሐመድ፣የውሃ፣ መስኖና እና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትርን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት እንዲሁም የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተርና የአካባቢው ነዋሪዎች ተገኝተዋል።