ዓለምአቀፋዊ ዜና

ትራምፕ ወደ ስራ ለመመለስ ዝግጁ መሆናቸውን ሃኪሞች ተናገሩ

By Feven Bishaw

October 09, 2020

አዲስ አበባ ፣መስከረም 29፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ወደ ስራ ለመመለስ ዝግጁ መሆናቸውን ሃኪሞች ተናገሩ፡፡

ትራምፕ ባለፈው ሳምንት ኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸው ሆስፒታል መግባታቸው የሚታወስ ነው፡፡

አሁን ላይ ፕሬዚዳንቱ የህክምና ክትትላቸውን ጨርሰው ከሆስፒታል የወጡ ሲሆን ወደ ስራ እንደሚመለሱም የግል ሀኪማቸው ተናግረዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ የቫይረሱን ምልክት እያሳዩ አለመሆኑም ነው የተነገረው፡፡

ይሁን እንጅ ትራምፕ ዛሬ የኮሮና ምርመራ ሊያደርጉ እንደሚችሉ ተናግረዋል፡፡

በትናንትናው እለት ለመጭው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ከተቀናቃኛቸው ጆ ባይደን ጋር በቪዲዮ ኮንፈረንስ ሁለተኛውን ክርክር እንዲያደርጉ የቀረበላቸውን ግብዣ ውድቅ ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡

በወቅቱ ትራምፕ በቪዲዮ ኮንፈረንስ በሚካሄድ ክርክር ጊዜየን አላጠፋም የሚል ምላሽ መስጠታቸውም አነጋጋሪ ሆኖ ነበር፡፡

ምንጭ፡-ቢቢሲ