የሀገር ውስጥ ዜና

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤና አመራሮች የምርጫ ቦርድን የምርጫ ዝግጅት ጎበኙ

By Feven Bishaw

October 09, 2020

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 29፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎና የምክር ቤት አመራሮች የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የምርጫ ቅድመ ዝግጅትን ጎብኝተዋል፡፡

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስድስተኛው ሃገር አቀፍ ምርጫ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የመከላከያ መንገዶችን በመተግበር እንዲካሄድ ከጤና ሚኒስቴር የቀረበለትን ምክረ ሃሳብ በተጨባጭ በማጤን መወሰኑ ይታወሳል።