ዓለምአቀፋዊ ዜና

በብራዚል በኮሮና ቫይረስ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር ከ150 ሺህ በላይ ሆነ

By Meseret Awoke

October 11, 2020

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 1፣ 2013(ኤፍ.ቢ.ሲ)በብራዚል በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ከ150 ሺህ በላይ ሆኗል።

ብራዚል ከአሜሪካ በመቀጠል በዓለም ከፍተኛ በኮሮና ቫይረስ የሞቱ ሰዎች ያሉባት ሃገር ሆናለች።

ከዚህ ባለፈም ከአሜሪካ እና ህንድ ቀጥሎ በከፍተኛ ደረጃ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ያሉባት ሃገር በመሆን በሦስተኛ ደረጃ ተቀምጣለች።

በሃገሪቱ በሳምንቱ መጀመሪያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 5 ሚሊየንን መሻገሩ የሚታወስ ሲሆን የሃገሪቱ ፕሬዚዳንት የባለሙያዎችን ምክር ወደጎን ማለታቸው ለቫይረሱ መስፋፋት ምክንያት መሆኑ ይነሳል።

ደቡብ አሜሪካዊቷ አገር ብራዚል እስካሁን 5ሚሊየን 82 ሺህ 600 በላይ ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ ከ150 ሺህ 190 በላይ ሰዎች ለህልፈት ተዳርገዋል።

ዓለምበ ላይ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥርም ከ37 ሚሊየን 475 ሺህ በላይ ሲሆን ህይዎታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ደግሞ ከ1 ሚሊየን 77 ሺህ በላይ ሆኗል።

በአንጻሩ ከ28 ሚሊየን 117 ሺህ በላይ ሰዎች ከቫይረሱ አገግመዋል።

ምንጭ፡- ቢ.ቢ.ሲ እና ዎርልድ ኦ ሜትር