የሀገር ውስጥ ዜና

ሃገር አቀፍ የብስክሌተኞችና የእግረኞች ቀን በአዲስ አበባ በተለያዩ ዝግጅቶች ተከበረ

By Meseret Awoke

October 11, 2020

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ሁለተኛው ሃገር አቀፍ የብስክሌተኞችና የእግረኞች ቀን በአዲስ አበባ በተለያዩ ዝግጅቶች ተከበረ።

ቀኑ “ደህንነቱ የተጠበቀ መንገድ ለእግረኞችና ለብስክሌተኞች” በሚል መሪ ቃል ነው የተከበረው።

እለቱ የሞተር አልባ የትራንፖርት እንቅስቃሴዎች የትራፊክ አደጋ ተጋላጭነትን ለመቀነስ ግንዛቤን የማደሳደግ ዓላማ በማድረግ መከበሩን የትራንስፖርት ሚኒስትሯ ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ ተናግረዋል፡፡

በሁሉም የክልል ከተሞች ወር በገባ በመጨረሻው እሁድ የብስክሌተኞችና የእግረኞች ቀን ፕሮግራም ላይ የሞተር አልባ የትራንስፖርት አማራጭን ፋይዳ በመረዳት ሁሉም ዜጋ ተሳታፊ እንዲሆንም ጥሪ ቀርቧል፡፡

አያይዘውም ሁሉም በአካባቢው በመሳተፍ ለትራፊክ አደጋ የማያጋልጥ የመንገድ ላይ እንቅስቃሴ እንዲኖር እና አደጋው እንዲቀንስ የበኩሉን እንዲወጣ መጠየቃቸውን ከትራንስፖርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።