የሀገር ውስጥ ዜና

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ተመሥገን ጥሩነህ በደቡብ ጎንደር ዞን በኩታ ገጠም የለማ የጤፍ ማሳን ጎበኙ

By Abrham Fekede

October 12, 2020

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ተመሥገን ጥሩነህ በደቡብ ጎንደር ዞን በኩታ ገጠም የለማ የጤፍ ማሳን ጎበኙ፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ በደቡብ ጎንደር ዞን እስቴ ወረዳ ዝጎራ ቀበሌ ነው ጉብኝቱን ያደረጉት፡፡

የደቡብ ጎንደር ዞን ዋና አሥተዳዳሪ ቀለመወርቅ ምህረቴን ጨምሮ ሌሎች የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችም ተገኝተው በመኸር እርሻ የለማውን የኩታ ገጠም የጤፍ ማሳ መመልከታቸውን አብመድ ዘግቧል።

የጤፍ ማሳዎቹ የተሻሻሉ ዝርያዎችና ለአርሶ አደሩ የዘር ብዜት የሚጠቅሙ መሆናቸው ተገልጿል።