የሀገር ውስጥ ዜና

ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ በኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ሱዳን እና ደቡብ ሱዳን የዓለም ባንክ ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

By Tibebu Kebede

October 12, 2020

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 2 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ በኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ሱዳን እና ደቡብ ሱዳን የዓለም ባንክ ዳይሬክተር ኦስማን ዲዮን ጋር ተወያዩ፡፡

ከኦስማን ዲዮን በተጨማሪም በኢትዮጵያ ካሉት የዓለም ባንክ አመራሮች ጋር የከተማዋን መሰረታዊ ችግሮች በአጋርነት ለመፍታት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት አካሄደዋል።

በውይይታቸውም ዓለም ባንክ የከተማዋን ራዕይ ለማሳካት እየተሰሩ ያሉ ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎች በተለይም የውሃ፣ የመኖሪያ ቤት፣ የትራንስፖርት፣ የመሬት አስተዳደርና የስራ እድል ፈጠራ ላይ ቅድሚያ በመስጠት የከተማ አስተዳደሩን ለማገዝ ቁርጠኛ መሆናቸውን ዳይሬክተሩ መናገራቸውን ከአዲስ አበባ ከተማ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡