አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 6 ሺህ 344 የላቦራቶሪ ምርመራ 582 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 85 ሺህ 718 መድረሱንም ሚኒስቴሩ ያወጣው እለታዊ መረጃ ያመለክታል።
ከዚህ ባለፈም የ4 ሰዎች ህይወት በቫይረሱ ምክንያት ያለፈ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 305 መድረሱንም የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ አመላክተዋል።
በሌላ መልኩ በትናንትናው እለት 403 ሰዎች ከኮሮና ቫይረስ ያገገሙ ሲሆን፥ በአጠቃላይ ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 39 ሺህ 307 መድረሱም ተገልጿል።
ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ እስካሁን ለ1 ሚሊየን 362 ሺህ 947 ሰዎች ምርመራ የተደረገ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 85 ሺህ 718 ደርሷል።
አሁን ላይ ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች ቁጥር 45 ሺህ 104 ሲሆን፥ ከእነዚህም ውስጥ 237 ሰዎች በጽኑ የታመሙ መሆናቸውንም የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።
እስካሁን በኢትዮጵያ 39 ሺህ 307 ሰዎች ከቫይረሱ ሲያገገሙ፤ የ1 ሺህ 305 ሰዎች ህይወት አልፏል፤ 2 ሰዎች ወደ ሀገራቸው መመለሳቸው ይታወሳል።
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።