የሀገር ውስጥ ዜና

የመገናኛ ብዙኀን ብዝሃነት ቢፈጠርም የጋዜጠኞች መረጃ የማግኘት መብት ግን አሁንም ችግር ውስጥ እንደሚገኝ ተገለጸ

By Abrham Fekede

October 14, 2020

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ባለፉት ሁለት የለውጥ ዓመታት በሃገሪቱ የመገናኛ ብዙሃን ዘርፍ ውስጥ የመገናኛ ብዙኀን ብዝሃነት ቢፈጠርም የጋዜጠኞች መረጃ የማግኘት መብት በአንጻሩ አለመከበሩ ተገለጸ።

ይህ የተገለጸው የኢትዮጵያ ፖሊሲ ጥናት ኢንስትቲዩት ባዘጋጀው በሃገሪቱ የተሃድሶ፣ ሚዲያ እና የህግ የበላይነት መድረክ ላይ የሚዲያው ዕድልና ተግዳሮቶች በተዳሰሱበት ወቅት ነው።

የመገናኛ ብዙኀን አስተዳደር ህግና ፖሊሲዎች እንዲሁም መሰል ማሻሻያዎች በመካሄድ ላይ ቢሆኑም በፍጥነት ወደ ተግባር ባለመግባታቸው ውስንነቶች እንዳሉም በመድረኩ ተነስቷል።

በሃገሪቱ የመገናኛ ብዙኀን ዘርፍ የለውጥና የብዝሃነት ዕድል በተፈጠረበት የመረጃ ነጻነት አዋጅ መውጣቱንና የመገናኛ ብዙኀን ፖሊሲ መጽደቁንም ብሮድካስት ባለስልጣን ጠቅሷል።

መድረኩ በመገኛኛ ብዙኀን ባለቤትነትና እድገት ላይ እንዲሁም በህግና ፖሊሲ አተገባበር ላይ መደረግ ይገባዋል ያለውን ምክረ ሃሳብም አቅርቧል።

 

 

በተስፋዬ ከበደ