የሀገር ውስጥ ዜና

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 665  ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተያዙ

By Feven Bishaw

October 16, 2020

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 6 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 6 ሺህ 569 የላቦራቶሪ ምርመራ 665 ሰዎች ኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 87 ሺህ 834 ደርሷል።

በሌላ በኩል በትናንትናው ዕለት 640 ሰዎች ከቫይረሱ ሲያገግሙ ይህን ተከትሎ በአጠቃላይ ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 41 ሺህ 628 መድረሱንም አስታውቋል።

በተጨማሪም ባለፉት 24 ሰአታት የ12 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በቫይረሱ ሳቢያ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 337 ደርሷል።

በአሁኑ ወቅት ቫይረሱ ካለባቸው 44 ሺህ 867 ሰዎች መካከል 301 ያህሉ በጽኑ ሕክምና ላይ መሆናቸው ተገልጿል።

በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ለ1 ሚሊየን 383 ሺህ 649 ሰዎች የኮሮናቫይረስ የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጓል።