የሀገር ውስጥ ዜና

የኦሮሚያ ክልል የመንግስትና የብልጽግና ፓርቲ የሩብ ዓመት የስራ አፈጻጸም እየተገመገመ ነው

By Tibebu Kebede

October 19, 2020

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 9 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል የመንግስትና የብልጽግና ፓርቲ የሩብ ዓመት የስራ አፈጻጸም በአዳማ ከተማ እየተገመገመ ነው፡፡

የስራ አፈጻጸም ግምገማው ላይ የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ የኦሮሚያ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፍቃዱ ተሰማ፣ የክልሉ የቢሮ ኃላፊዎች እንዲሁም የዞንና የከተማ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡

የስራ አፈጻጸም ግምገማው ለሶስት ቀናት እንደሚቆይ የኢቢሲ ዘገባ ያመላክታል፡፡