የሀገር ውስጥ ዜና

አዲስ ለተገነቡ የጋራ መኖሪያ ቤቶች የተዘረጋን የኤሌክትሪክ መስመር የሰረቁ ተጠርጣሪዎችን እጅ ከፍንጅ መያዙን ፖሊስ አስታወቀ

By Tibebu Kebede

October 20, 2020

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 10 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲስ ለተገነቡ የጋራ መኖሪያ ቤቶች የተዘረጋን የኤሌክትሪክ መስመር የሰረቁ ሦስት ተጠርጣሪዎች እጅ ከፍንጅ ተይዘው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን የቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል፡፡

ሦስቱ ተጠርጣሪዎች የወንጀል ድርጊቱን የፈፀሙት በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ልደታ ሣይት አዲስ ከተገነቡ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ውስጥ ነው፡፡

ግለሰቦቹ በሣይቱ ለመኖሪያነት ከተገነቡት ህንፃዎች መካከል 500 ሺህ ብር የሚያወጣ የአንዱን ህንፃ የኤሌክትሪክ ኬብል ቆርጠው ለማምለጥ ሲሞክሩ በፖሊስ አባላት እጅ ከፍንጅ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡