የሀገር ውስጥ ዜና

134 ኢትዮጵያውያን ከቤሩት ተመለሱ

By Meseret Demissu

October 21, 2020

አዲስ አበባ ፣ጥቅምት 11፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) 134 ኢትዮጵያውያን ዜጎች ዛሬ ጠዋት ከቤሩት ተመልሰዋል።

ቦሌ ዓለም አቀፍ አወሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሴቶችና ህጻናት ፅህፈት ቤት  ዳይሬክተር ጄኔራል ወይዘሮ አልማዝ ገበያው እና የሚመለከታቸው የመስሪያ ቤት የስራ ሃላፊዎች በቦታው ተገኝተው አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ኢትዮጵያውያኑ በዘጠነኛው ዙር የማስመለስ ፕሮግራም አማካኝነት የተመለሱ መሆናቸው ተነግሯል።

በዘጠነኛው ዙር የማስመለስ ፕሮግራም በአጠቃለይ 3 ሺህ 289 ኢትዮጵያውያን ዜጎችን ከሊባኖስ ለመመለስ የሚያስችል ዝግጅት ተጠናቆ ወደ ስራ መገባቱን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።