የሀገር ውስጥ ዜና

የፌዴሬሽን ምክር ቤት በ15ኛው የብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን አከባበር ዙሪያ እየመከረ ነው

By Abrham Fekede

October 21, 2020

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የፌዴሬሽን ምክር ቤት በ15ኛው የብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን አከባበር ዙሪያ እየመከረ ነው፡፡

ምክር ቤቱ በአከባበሩ ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ነው በአዳማ እየመከረ የሚገኘው፡፡

ከሳምንት በፊት ምክር ቤቱ በዘንድሮው የብሄር ብሄረሰቦች በዓል ላይ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የአከባበር ለውጥ እንደተደረገበት ማስታወቁ የሚታወስ ነው፡፡

ይህን ተከትሎም ከዚህ ቀደም በአንድ ክልል አዘጋጅነት የሚከበርበት መንገድ ቀርቶ ከኅዳር 15 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ በወጣ መርሀ ግብር በየክልሉ እንደሚከበርም ነበር ያስታወቀው፡፡